Uncategorized

የሞባይል ባትሪ እድሜ እንደት መጨመር ይቻላል?

የሞባይል ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል ወይም ቶሎ እንዲበላሽ የራሳችን የአጠቃቀም ሁኔታ ይወስነዋል። ምን አልባት አንዳንድ ሰዎች ባትሪን ቶሎ እንሞላለን ፣ እንዳይጨርስ እናደርጋለን የሚሉ አሉ። እሱ ስህተት ነው ፣ በአቋራጭ የሚሆን ነገር የለም፤ ትክክለኛውን እና ሳይንሳዊ የሆነውን መንገድ ብቻ ከተከተልን የሞባይላችን ባትሪ የአገልግሎት/ የቆይታ ጊዜ ማራዘም እንችላለን።
ባትሪ እንዳይሞትብን ወይም እንዳይደርቅብን ከፈለግን የሚከተሉትን አስር የጥንቃቄዎች መንገዶች መተግበር አለብን።

ማስታወሻ፡ በዚህ ፅሁፍ የተቀመጡት ነጥቦች ባላቸው ጥቅም መሰረት በቅደም ተከተል የተቀመጡ አይደሉም። ይልቁንስ ሁሉም የየራሳቸው እኩል አስተዋፅኦ ስላላቸው በተቻለ መጠን ሁሉንም በመተግበር የበለጠ የባትሪአችን እድሜ ማራዘም እንችላለን።

https://youtube.com/watch?v=bJPLY1OH53s%3Fstart%3D33%26feature%3Doembed

  1. የባትሪያችን ቻርጅ በአማካኝ 50% ወይም በላይ ሆኖ እንድቆይ ማድረግ፡
    በተቻለ መጠን የባትሪያችን ቻርጅ ከ40% እስከ 80% ማድረግ የባትሪ እድሜ ይጨምራል። ምንም እንኳ መሙያው (charger) ከመጠን በላይ እንዳይሞላ (ቻርጅ እንዳያደርግ) እና እንዳይጎዳ የመቆጣጠሪያ እትብት (Control
    circuit) ቢኖረውም ፤ ባትሪያችን 100% ከሆነ በኋላ መንቀል እና ሌሊቱን በሙሉ ቻርጅ አለማድረግ ጥሩ ነው።
  2. ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ፡
    ባትሪን 0% ከሆነ በኋላ እንደገና 100% ከማድረግ ይልቅ በቀን ውስጥ ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ ባትሪያችን እንዳይደርቅ/እንዳይበላሽ ውጤታማ አስተዋፅኦ አለው። ሁሉም ባትሪዎች ተመሳሳይ ባህሪ የላቸውም። የተለያዩ ባትሪዎች የተለያየ ቻርጅ የሚደረጉበት ጊዜ አላቸው። ነገር ግን ሁሉም ባትሪዎች ቀስበቀስ እየሞቱ ይሄዳሉ። ሁልጊዜም ባትሪው ሳይጨርስ መሙላት ጥቅም እንጅ ጉዳት የለውም። ቻርጅ ስናደርግ ደግሞ ሁልጊዜም ከሞባይሉ ጋር የተገዛውን ቻርጀር በመጠቀም ከግድግዳ ሶኬት መሆን አለበት። ከመኪና እና ከኮምፒውተር ቻርጅ ማድረግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል።
  3. የማንጠቀምባቸውን መተግበሪያዎች ማጥፋት፡
    Airplane Mode የባትሪያችን ጓድኛ ነው። ሁሉንም ከሞባይላችን የሚወጡ እና የሚገቡ የሬድዮ ሲግናሎች ያቋርጣል፤ ጥሪዎች፣ መልክቶች፣ ብሉቱዝ፣ ኢሜይል፣ ዋይፋይ እና ሌሎችም ስራቸው እንድቋረጡ ያደርጋል። ምናልባት airplane Mode መጠቀም ምንም ነገር ስለማያስጠቅመን ሁሉንም ማጥፋት ተገቢ ላይሆን ይችላል ስለሆነም
    የማንጠቀምባቸው ከሆኑ የተወሰኑትን ብቻ Bluetooth, Wi-Fi, GPS, and NFC እያንዳንዳቸውን ማጥፋት የባትሪያችን እድሜ ይጨምራል።
    አንዳንድ ሰው የማይጠቀምባቸውን መተግበሪያዎች ሞባይሉ ውስጥ ያስቀምጣል፣ አልፎም ያበራቸዋል፤ ለምሳሌ ሁልጊዜም የአቅጣጫ መጠቆሚያ የማያስፈልገን ከሆነ GPS ማብራት ባትሪያችን ከመጨረስ ውጭ ምንም ጥቅም የለውም። ስንፈልግ ብቻ ማብራት ባትሪ እንድንቆጥብ ያግዘናል።
  4. መተግበሪያዎችን ማሻሻል እና ሞባይላችን ማፅዳት:
    የመተግበሪያዎቻችን ማሻሻያዎች ሲለቀቁ ቶሎቶሎ ማሻሻል የሜሞሪ እና ባትሪያችን አጠቃቀም ያሻሽላል። ሁሉንም ሳይሆን ሁልጊዜ የምንጠቀምባቸውን እና የምንፈልጋቸውን መተግበሪያዎች ብቻ እናሻሽል። በተጨማሪም የሞባይላችን አላስፈላጊ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ ማፅዳት የባትሪ እድሜን ያረዝማል።
  5. ጥቁር/ደብዛዛ wallpaper እንጠቀም፡
    ብዙ ሰዉ ተንቀሳቃሽ ምስል የሞባይሉ እስክሪን ሽፋን ያደርጋል፣ ይህ ልምድ ባትሪን ይጎዳል። ጥቁር የእስክሪን መሸፈኛ መጠቀም የባትሪ እድሜን ያረዝማል ምክንያቱም ስክሪናችን ቀለም ያላቸው ፒክስሎችን ብቻ ነው እሚያበራው። ጥቁር ፒክስሎች ፈዛዛ እና ምስል ለመፍጥር ትንሽ ሃይል የሚጠቀሙ ናቸው፣። ስለዚህ ጠቆር ያለ እና የማይንቀሳቀስ ምስል መጠቀም ባትሪ ይቆጥባል።
  6. ደብዛዛ ስክሪን፡
    ብርሃኑ የበዛ ስክሪን ባትሪ ከመጨረሱ በተጨማሪ አይንን ይጎዳል። ስለሆነም በተቻለ መጠን የሞባይላችን ብርሃን (brightness) መቀነስ ለአይናችን እና ባትሪያችን ጤንነት ጠቃሚ ነዉ።
  7. ባትሪ መቆጠቢያ መተግበሪያዎችን መጠቀም፡
    ብዙ የባትሪ መቆጠቢያ እና መቆጣጠሪያ መተግበሪያዎች ሲኖሩ ዋና ጥቅማቸው ባትሪን ያለአግባብ የሚጭርሱ ሃርድዌር እና ሶፍትዌሮችን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድሰሩ ማስቻል ነው። እነዚህ መተግበሪያዎች የትኛው መተግበሪያ ብዙ ባትሪ እንደተጠቀመ የሚያመለክቱ፣ የትኛውን ማጥፋት ወይም ማብራት እንዳለብን የሚያሳዩ፣ የባትሪ አጠቃቀም መረጃ የሚሰጡ ፣ ስለባትሪያችን የጥንቃቄ ማስታወሻ የሚሰጡ ፣ ወዘተ ጥቅም አላቸው።
  8. ማስታወሻዎችን (notifications) ማጥፋት:
    ማስታወሻዎች በእለትተለት እንቅስቃሴአችን አስፈላጊ ቢሆኑም ባትሪ ግን ይበላሉ፣ በተለይም ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ፣ የማህበራዊ ሚድያ፣ የኢሜይል፣ የአየር ንብረት ወዘተ ማስታወሻዎች የባትሪን እድሜ ያሳጥራሉ። ስለዚህ አላስፈላጊ ማስታወሻዎችን በማጥፋት ባትሪን መቆጠብ ይቻላል።
  9. አላስፈላጊ እርግብግቢትን (vibrate) እና ራሳቸዉን የሚያሳድጉ መተግበሪያዎችን ማጥፋት፡
    ራሳቸዉን የሚያሳድጉ መተግበሪያዎች ጥሩ ቢሆኑም ባትሪ ይጨርሳሉ፣ ስለዚህ መምረጥ ያስፈልጋል። በተመሳሳይ እርግብግቢት ባትሪ ይጨርሳል።
  10. ከመጠን በላይ መሞቅ እና መቀዝቀዝ:
    በከፍተኛ ሙቀት ቻርጅ ማድረግ እና ማስቀመጥ ባትሪን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል። ባትሪ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራበት የሙቀት መጠን ሰፊ ወሰነ ገደብ ሲኖረው ከ62 እስከ 72 ፋራናይት ጥሩ የሚባለው ነዉ። ከ95 ፋራናይት በላይ መጠቀም ሙሉ በሙሉ ባትሪውን ይጎዳዋል፣ ድጋሜ አገልግሎት መስጠትም አይችልም!። በጣም ቀዝቃዛ በሆነ ሙቀት መጠቀምም ባትሪን በጊዜአዊነት የሚገል ሲሆን ነገር ግን ሙቀቱ ሲስተካከል ባትሪው ወደነበረበት ሊመለስ ይችላል።

Note: Whenever you are looking for a job in Ethiopia, just remember https://jobs.amazonethiopia.com. We hope that jobs.amazonethiopia.com will help you find your dream job quickly and easily.

የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን (social media) አባል ነዎት?
ካልሆኑ ወደፊት የምናወጣቸው የስራ እና ጨረታ ማስታወቂያዎች እንዳያመልጠዎ የቴሌግራም ገጻችን እና የፌስቡክ ገጻችን ይወዳጁ! ለሌሎችም ያጋሩ! በጎነት ለራስ ነው!
ቴሌግራም: https://t.me/amazonethiopiajobs
ፌስቡክ፡ https://fb.me/tikusjobs
ድረ ገፅ፡ jobs.Amazonethiopia.com


እስካሁን ድረስ ያነሳዋቸው ነጥቦች ግልፅ ካልሆኑ ወይም ጥያቄ ካላችሁ አስተያየት መስጫው ላይ ብትፅፉ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።
መረጃውን ከወደዳችሁት ደግሞ ለወዳጆቻችሁ አጋሩ፤ ገፁን ተወዳጁ።
ተጨማሪ የቴክኖሎጅ መረጃዎችን ከፈለጋችሁ ደግም https://technology.amazonethiopia.com/blog ውስጥ ቴክኖሎች አምድን መጎብኘት ይቻላል።

ስለአነበባችሁልኝ አመሰግናለሁ!
መመሪያዎቹን በማንበብ ብቻ ሳይሆን በመተግበር የሞባይል ባትሪን እድሜ እንጨምር! የአካባቢ ብክለትን እንቀንስ!

Related posts

Leave a Comment

0
YOUR CART
  • No products in the cart.